Dessie

 የአብክመ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እና በስነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ ለመቅረጽ ያለመ ሰፊ የስልጠና መድረክ በደሴ ከተማ ተካሄደ።

የመድረኩን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደሴ ከተማ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ፍቅር አበበ እንደገለጹት ትምህርት የወደፊት ሀገራዊ ለውጥና የነገዋ ሀገር ተረካቢ ትውልድ መቅረጫ ዋና መሰረት መሆኑን ጠቁመው፤ እንደ ሀገር ያሉትን ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች፣ የሌብነት፣ የእድገት ወደኋላ ቀርነትና የሰላም እጦት ችግሮችን ዘላቂ በሆነ መልኩ መፍታት የሚቻለው በትምህርትና የአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣት ብቻ መሆኑን አስምረውበታል።
ስልጠናው የተዘጋጀው የደሴ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የደሴ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር ነው።
በመድረኩ ላይ ከደሴ ከተማ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ ርዕሳነ መምህራን እና የሥነ-ምግባር ክበብ አስተባባሪ መምህራን የተሳተፉ ሲሆን፣ “ለሀገር ተረካቢ ትውልድ የሥነ-ምግባር ግንባታ የትምህርት መዋቅሩ ሚና” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።
በአብክመ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የስነ-ምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ትምህርትና ስልጠና ባለሙያ አቶ ሀብታሙ አሰፋ “ለሀገር ተረካቢ ትውልድ የሥነ-ምግባር ግንባታ የትምህርት መዋቅሩ ሚና” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል።
የአብክመ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የምሥራቅ አማራ ደሴ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም አያሌው፣ የአሠራር ሥርዓት ጥናቶች ተቋማት በሕግና በመርህ መሠረት እንዲሠሩ፣ ከብልሹ አሠራር እንዲጠበቁና የአፈጻጸም ክፍተቶችን በወቅቱ እንዲያርሙ የሚያግዙ ወሳኝ መሣሪያዎች መሆናቸውን አስገንዝበዋል።
በውይይቱ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱና የኩታበር ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ጽሕፈት ቤት የማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል።
የተማሪዎችን የሥነ-ምግባር ክበባት በማጠናከር ከሙስናና ከብልሹ አሠራር የጸዳ ትውልድ ለመገንባት እየተሠራ ነው ተባለ!
በመድረኩም የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት አመራሮች፣ ባለሙያዎች፣ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ተሳትፈዋል
የሥነ-ምግባር ግንባታ፣ የሀብት ምዝገባና ማጣራት፣ የአሠራር ሥርዓት ማሻሻያ እንዲሁም በሙስናና በብልሹ አሠራር የሚሳተፉ አካላትን ከፍትሕ ተቋማት ጋር በቅንጅት ተጠያቂ የማድረግ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ይህንኑ ተግባር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በተቀናጀ መልኩ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመልክተዋል።
የአብክመ ሥነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን የምስራቅ አማራ ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ ከሲቪክ ማህበራት፣ ከእምነት ተቋማትና ከሙያ ማህበራት አመራሮች ጋር በትውልድ ሥነ-ምግባር ግንባታና በጸረ-ሙስና ትግል ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
ቅርንጫፋችን በክልል ደረጃ 1ኛ ስለ ወጣ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስስስ አለን።የጋራ ውጤት በመሆኑ ከደረጃችን እንዳንቀንስ በ2019 በጀት ዓመትም የበኩላችን ሚና መወጣት ይኖርብናል።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ደሴ ቅርንጫፍ የ9 ወር ተቋማዊ እቅድ አፈጻጸሙን እየገመገመ ነው።